|
የስዊድን ኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ
(ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)
በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ ሙሉ ለሙሉ ተዳፍኗል የሰው ልጅ በሰውነቱ ሊያገኛቸው የሚገባው መብቶች ሁሉ ኢትዮጵያ ላይ የሉም። ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሰማው ነገር የለውም እንኳን በሃገሩ የሚፈጸመውን ይቅርና የጎረቤቱን ሁኔታ እንኳን እንዳይሰማ ታፍኗል። ነጻ ጋዜጠኖች በነቂስ እየተለቀሙ ታስረዋል ይበልጦቹ ተሰደዋል።
ይሄን ለመታደግ የተቋቋመው ኢሳት ብዙ ገንዘብ ለአፈና እየተመደበለት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታይ ቢደረግም አገልግሎቱን በልዩ ልዩ መልክ እንዲዳረስ እያደረገ ነው ለ ሀያ አራት ሳአት የማያቋርጥ የራድ ዝግጅት እያደረገ ወደ ኢትዮጵያ በማስተላለፍ ላይ ይገኛል። የሞባይል ቴሌፎን ተጠቃሚ የሆነም የውጪ ነዋሪ አገልግሎቱን ሊጋራ ችሏል። ቲሌቪዚኑም ወደ ሃገር ቤት እንዲገባ ተጨማሪ ጥረት እያደረገ ነው።
ስለዚህ አማራጭ ላጣው የሃገራችን ህዝብ ኢሳት እውነተኛ የመረጃ ምንጭ ስለሆነ እንዲሁም በሃገራችን ለዲሞክራሲና ለነጻነት ለሚደረገው ትግል አስተዋጽዖ እያደረገ ስለሚገኝ ማንኛውም ሀገር ወዳድ ሁሉ ኢሳትን መደገፍ ይገባዋል።
ኢሳት ይሄንን በተመለከተ በድህረ ገጹ ላይ ያሰፈረውን መረጃ መረዳት ስለኢሳት ይበልጥ ለማውቅ ያስችላል። ኢሳት የህዝብ አይንና ጆሮ በመሆኑ እንርዳ።
|