ዋና ገጽ መጻሕፍት
 
መጻሕፍት

የዓለማየሁ ታዬ አዲስ የልጆች መጽሐፍ Print E-mail
User Rating: / 10
PoorBest 

Betsy and the Supercopter - By Alemahehu Tayeዓለማየሁ ዲባባ

ለልጆች ከሚዘጋጅ ጽሑፍ አኳያ ሲዳሰስ

ዓለማየሁ ታዬ ገጣሚ፣ ተርጓሚና ጋዜጠኛ ነው። ከዚህ ቀደም በአይነታቸውና በይዘታቸው ልዩ የሆኑ ሦስት የግጥም መድብሎችን እንዲሁም የልጆች መጻሕፍት ተርጉሞ ለሕትመት አብቅቷል። በቅርቡ ደግሞ ወጥ የሆነ አንድ የልጆች መጽሐፍ በእንግሊዝኛ ቋንቋ አሣትሟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የበረከት መጽሐፍ Print E-mail
User Rating: / 7
PoorBest 

የሁለት ምርጫዎች ወግ Yehulet Mirchawoch Wog ተስፋዬ ገብረአብ This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it

የበረከትን መጽሐፍ አነበብኩት …

በእውነቱ ህትመቱ ቆንጆ ነበር። ሽፋኑ እንደ ሃብታም ጉንጭ ይለሰልሳል። ከቻርልስ ዲክንስ ታዋቂ መጽሐፍ የተኮረጀ ቢሆንም ርእሱም ቢሆን አሪፍ ነው - የሁለት ምርጫዎች ወግ። የበረከትን መጽሐፍ ያሳተመው መሐመድ አሊ አልአሙዲ የተባለው ነጋዴ መሆኑን ፍትህ ጋዜጣ ላይ አንብቤ ነበር። መጽሐፉ 314 ገፆች እና 10 ምዕራፎች ይዞአል። ዋጋው 90 ብር ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የሁለቱ ‹‹ኢህአፓ››ዎች ጉራማይሌ ወግ (በረከት ስምኦን እና ብርሃኑ ነጋ) Print E-mail
User Rating: / 7
PoorBest 

ተመስገን ደሳለኝ

ከኢህአፓ ወደ ኢኮፓ፤ ከኢኮፓ ወደ ኢህዴን፤ ከኢህዴን ወደ ብአዴን… እነዚህ ሁሉ የዛሬው እንግዳችን የፖለቲካ ዝውውሮች ናቸው። መቼም ‹‹በዚህ ትውልድ›› ዝውውር ተፈፀመ ወይም ተዘዋወረ ከተባለ ከማንችስተር ዩናይትድ ወደ ሪይል ማድሪድ፤ አሊያም ከአርሰናል ወደ ባርሴሎና ነው። ‹‹በያ ትውልድ›› ደግሞ ከአንዱ ፓርቲ ወደ ሌላው ፓርቲ፤ ከሶሻሊዝም ወደ ካፒታሊዝም፤ ከኢምፔሪያሊዝም ወደ ኮሚኒዝም፤ ከአልባኒያኒዝም ወደ ማሌሊትዝም፤ ከማሌሊትዝም ወደ አብዮታዊ ዲሞክራቲሲዝም … ሲሆን ይሄ አይነቱ ዝውውር ‹‹የብልህ›› ስልት ተደርጎ ከመወሰዱም ባሻገር ለተዘዋዋሪዎቹ ጫማ ከመቀየር የቀለለ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የሸራተኑ ምሽት - በአቶ በረከት መጽሐፍ Print E-mail
User Rating: / 12
PoorBest 

የሁለት ምርጫዎች ወግ Yehulet Mirchawoch Wogአዲስ አድማስ ጋዜጣ

- አቶ በረከትና ሼኽ መሐመድ አሊ አልአሙዲ የተደናነቁበት ምሽት

- አቶ መለስ፣ ኢህአዴግና አልአሙዲ ተወድሰዋል

- ኢህአዴግ “የሕዝብ ፍቅር ያለው ፓርቲ” ተብሏል

- በመጽሐፉ ተቃዋሚዎች ክፉኛ ተተችተዋል - በተለይ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

የኢህአዴግ ነባር ታጋይ፣ የቀድሞው የማስታወቂያ ሚኒስቴር፤ አሁን ደግሞ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር እንዲሁም በምርጫ 97 ጉልህ ስፍራ የነበራቸው አቶ በረከት ስምኦን ጻፉት የተባለውን መጽሐፍ ለማንበብ በጉጉት ስጠባበቅ ነበር። ባለፈው ማክሰኞ በመጽሐፉ ምረቃ ላይ ለመታደም ወደ ሸራተን አዲስ ሆቴል ያመራሁትም ከዚህ ጉጉት በመነጨ ስሜት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የነፃነት ጎህ ሲቀድ (የመጸሐፍ ቅኝት) በመስፍን ማሞ ተሰማ Print E-mail
User Rating: / 8
PoorBest 

Yenestanet Goh Siked የነፃነት ጎህ ሲቀድጠሀፊ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

ቅኝት መስፍን ማሞ ተሰማ

የቅኝት ትኩረት - በአሰብ ጥያቄ ዙሪያ

መንደርደሪያ

የነፃነት ጎህ ሲቀድ በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ህዝባችን ለዴሞክራሲያዊና መልካም አስተዳደር መቆም ያደረገውን ልዩና ታላቅ የተጋድሎ ታሪክ በታሪክ መዘክርነት ያቀረበ ታሪካዊ መጥሀፍ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 
«StartPrev12345NextEnd»

Page 1 of 5

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 


ኢሳትን ይርዱ!