Home መጣጥፍ አስተያየት የብሔር (ጎሣ) ግጭት መንስዔዎችና መፍትሔዎቹ
የብሔር (ጎሣ) ግጭት መንስዔዎችና መፍትሔዎቹ Print E-mail
User Rating: / 5
PoorBest 
Articles
Tuesday, 19 August 2008 20:40

( ትንታኔ)

ከ81 በላይ የሆኑ ብሔሮች በኢትዮጵያ እንዳሉ ይታወቃል። እነዚህ ብሔር ብሔረሰቦች ለረዥም ዘመናት የቆየና የዳበረ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ትስስር እንደነበራቸውና እንዳላቸው እሙን ነው። በተቃራኒው ደግሞ በተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች መካከል ግጭቶች ሲከሰቱ ኖረዋል። በተለይ ከ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ ወዲህ ግጭቶቹ እየበረከቱ ስለመምጣታቸው ብዙዎች ይስማሙበታል።

 

በሀገር ውስጥ ከሚታተሙት ጋዜጦች አንዱ የሆነውና ነኀሴ 9 ቀን 2000 ዓ.ም. የተነበበው ”እንቢልታ” የተሰኘው ጋዜጣ በቅጽ 1፣ ቁጥር 34 እትሙ ”የብሔር (ጎሣ) ግጭት መንስዔዎችና መፍትሔዎቹ” በሚል ርዕስ የብሔር ግጭት አሁን ያለበትን ደረጃ መንስዔዎቹንና መፍትሔዎቹን በዘርፉ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ምሁራንን ሃሳብና ጽሑፎች በማካተት ትንታኔ አቅርቧል።

 

ጋዜጣው በዚህ ባስነበበው ጽሑፍ ላይ ”ብሔር (ብሔረሰብ) ጎሣ እና ግጭት”፣ ”መንስዔዎች”፣ ”የሕገ መንግሥቱና የፌደራል ሥርዓቱ አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎች”፣ ”ከብሔር ክልላቸው ውጭ የሚኖሩ ዜጐች ችግር” እና ”መፍትሔዎቹ” በሚሉ ንዑስ ርዕሶችን አካቷል። (የጋዜጣውን ሙሉ ትንታኔ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ) 

 

 
 

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ