ዋና ገጽ መጣጥፍ አስተያየት ይድረስ ለአቶ ግራማ ካሣ (ታምራት ታረቀኝ)
 
ይድረስ ለአቶ ግራማ ካሣ (ታምራት ታረቀኝ) Print E-mail
User Rating: / 1
PoorBest 

”በወዳጅህ ላይ ክፉ አትስራ፤ እርሱ ተማምኖ ከአንተ ጋር ተቀምጦ ሳለ” (መጽሐፈ ምሣሌ 3፤29)

ታምራት ታረቀኝ

አቶ ግራማ ካሣ ማንን እንደሚሞግቱ ለምንስ እንደሚሟገቱ የሚያውቁ አይመስልም። በሌሎች የሚሰጡ አስተያየቶችን በቅጡ አንብበው ጭብጡን ተረድተው ሊጽፉ ቀርቶ ከራሳቸው ሃሳብ ጋርም በወጥነት የሚዘልቁ ላለመሆናቸው አንድ ሁለት ጽሑፎቻቸውን ማየት ብቻ ይበቃል። በቀናት ልዩነት የሚጽፉት ቀርቶ በአንድ ቀን የሚጽፉዋቸው ሳይቀር እርስ በርስ የሚቃረኑ ለመሆናቸው ጽሑፎቻቸው ይመሰክራሉ።

 

ምርጫ ቦርድ የአንድነት ሊቀመንበር ኢ/ር ግዛቸው እንደሆኑ አድርጎ በድረ ገጹ አሰራጨ። የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ናትና ድርጊቱ የተፈጸመው በምርጫ ቦርድም ይሁን በእነ ኢ/ር ግዛቸው ሕጋዊ የሚሆንበት መሠረት የለውም ብዬ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ምዝገባ አዋጅና የአንድነትን መተዳደሪያ ደንብ ጠቅሼ ጻፍኩ። አቶ ግራማ የሰጡትና እየሰጡ ያለው አስተያየት ግን እኔ ካነሳሁት ጭብጥ ጋር የማይገናኝ ነው። የተቃውሞአቸው ምንክያት አልገባኝም። ነገረ ሥራቸው ሁሉ ”በምኒልክ ዘመን የደነቆረ ’ምኒልክ ይሙት!’ እንዳለ ይኖራል” ይሉ አይነት ነው። አቶ ግራማ የትናንት መነጽራቸውን አውልቀው በአዲስ መነጽር ጽሑፌን ቢያነቡትና በሚገባ ቢረዱት ስህተት የማይሰለቻቸው ቢሆንም የተሳሳተ ሃሳብ ከመሰንዘር ያድናቸው ነበር። … (... ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ! ...)

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 
Banner

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ