መጣጥፍ - Articles

የህዝብ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች መንታ መንገድ Print E-mail
User Rating: / 4
PoorBest 

ተመስገን ደሳለኝ

የመኢአድ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ታዲዮስ ቦጋለ የመኢአድ ሊቀመንበር በሆኑት ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል በተከሰሱበት ክስ ሁለት አመት ከስድስት ወር ተፈርዶባቸው ከርቸሌ ገቡ፤ መኢአድ እንደአንባሻ ተከፋፈለ፤ የማይለያዩት ኃይሉ ሻውል እና ማሙሸት አማረ ተለያዩ። አንድነት ፓርቲ ብርቱካን ሚደቅሳ ትፈታ ይል የነበረውን ጥያቄ አንዱአለም አራጌ ይፈታ በሚል ቀየረው፤ ብርቱካንን በማስብ ይበራ የነበረውንም ሻማ አንዷአለምን በማሰብ ይበራ ዘንድ ወሰነ፤ ብርቱካን ሚደቅሳ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ልታጠና ዋሽንግተን ሄደች፣ ስዬ አብርሃ ለትምህርት ወደአሜሪካ ሄዱ፤ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጀርመናዊ ህፃናቶችን ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊያስተምሩ ጀርመን ገቡ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

ሲዋን አዲስ መጽሀፍ (በጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ) Print E-mail
User Rating: / 4
PoorBest 

ስለ አሳዛኙ የኢትዮጵያዊያን የስደት ጉዞ፣ የበረሃና የውሃ ላይ ስቃይ የሚያስቃኝ ሊያነቡት ሚገባ አዲስ መጽሀፍ በገበያ ላይ ውሏል። ሲዋን አዲስ መጽሀፍ (በጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ)

 

 

ታሪክ ያላነበቡ ታሪክ ሰሪዎችና፣ ታሪክ ያላነበቡት ታሪክ ዘካሪዎች፣ ጉድ አፈሉብን! Print E-mail
User Rating: / 2
PoorBest 

ሰሎሞን ተሰማ ጂ. (ከአ.አ) - (ለፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በተለይ)

0. መግቢያ

ፍሬድርክ ኒቼ በደስታና በፈንጠዝያ የምፎልሉትን እንሰሳት ተጠጋና ጠየቃቸው። "ለምንድነው እንደዚህ ደስተኛ ልትሆኑ የቻላችሁት?" የሚል ነበር ጥያቄው። እነሱም ባንድነት፣ ባንድ ቃል መለሱለት። ምንም ሳይወያዩ፣ ምንም ነገር ሳይፎካከሩ፣ መንፍሳቸውም ሳይቀናና፣ አንዱም ሌላውን ሳይተች፣ ደመ-ነሳቸው በሚነግራቸው መሰረት፣ "ምንም ታሪክ (memory of things) ስለሌለን ነዋ!" አሉት። ከአፍታ በሁዋላ "ምን አላችሁኝ? እስኪ ድገሙልኝ?" ሲል ጥያቄዎቹን አጅጎደጎደባቸው። እነሱ ግን የሰጡት መልስ አጭርና አስገራሚ ነበር። "ምኑን ነው የምንደግምልህ?" የሚልና ክው አድርጎ የሚያስቀር መልስ። ሁሌም የሚደንቀኝ አይነት፣ "ቅስም-ሰባሪ" መልስ ይሉዋችሁዋል እንዲህ ያለው ነው-እንጂ! ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የሹክሹክታው ክፍል ሁለት ገፅታ Print E-mail
User Rating: / 2
PoorBest 

ተመስገን ደሳለኝ
ከዚህ ቀደም ‹‹ሹክሹክታው ምንድርነው?›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ አንድ ፅሁፍ ፅፌ ነበር። የፅሁፉ ጭብጥ የሚያጠነጥነው የአረብ ሀገራት የተሳካ አብዮትን ተከትሎ በኢትዮጵያም ሁለት ዓይነት ሹክሹክታዎች ነፍስ መዝራታቸው ላይ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

በፍትሕ ጋዜጣ ላይ ለምንጽፍ ሁሉ እየተናገሩ አለማነጋገር፣ እያሰቡ አለማሳሰብ Print E-mail

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

ይህ ጽሑፍ ለእኔም የተጻፈ በመሆኑ አንድ ቀልድ እንደመግቢያ ልናገር፤ አማኑኤል ሆስፒታል ሕመምተኛው ውጭ ይጽፋል፤ ሀኪሙ ይመጣና ‹‹ከበደ፣ እንደምናደርህ?›› ብሎት ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ፣ ሀኪሙ ምን እየጻፍክ ነው? ይልና ይጠይቃል፤ ህመምተኛው ‹‹ደብዳቤ›› ይላል፤ ሀኪሙ ‹‹ለማን ነው?›› ብሎ ሲጠይቅ፣ ሕመምተኛው ‹‹ለራሴ›› ይላል፤ ሀኪሙ የሕመምተኛውን የውስጥ ስሜት ለማወቅ ጓጉቶ ‹‹ምን ይላል?›› ብሎ ይጠይቃል፤ ሕመምተኛው በመደነቅ ዓይኑን በልጠጥ አድርጎ ‹‹ዶክተር መቼ ተላከና፣ መቼ ደረሰኝና!›› አለው፤ እኔም…

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የልማት ሠራዊት የሀገሪቱን አንጡራ ሀብት ሲያባክን Print E-mail
User Rating: / 1
PoorBest 

ኢንጂነር አብደልወሃብ ቡሽራ - መGለ

በትግራይ ክልል የልማት ሠራዊት እንዲሆኑ ተብለው የተመደቡ አካላት የወረዳና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች በሕወሓት ካድሬ መሪነት ነው እሚንቀሳቀሱት። የታዘዙትን የሚፈጽሙ ናቸው። እነዚህ አካላት የተሰማሩበት የሥራ ዓላማ በገጠር በተመረጡ ቦታዎች በመስኖ የሚለማ ግብርና ማፋጠን የሚል ነው። ለዚህ ተብሎ የታቀደው የልማት አቅጣጫ ደግሞ በተመረጡ የገጠር መንደሮች እያንዳንዱን ገበሬ በእርሻ ማሣው የውሃ ጉድጓድ መቆፈር እንዳለበት ነው። በተጨማሪ ከደደቢት የብድር ተቋም የውሃ ሞተር በብድር መልክ በመውሰድ ከጉድጓድ ውሃ እየመጠጠ ወደ እርሻ ማሳ እንዲጠያሰራጭ ታስቦ ነው። ለዚህ ጉዳይ የተመደበው ባጀት እንደሚከተለው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 
«StartPrev12345678910NextEnd»

Page 1 of 112

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 
Banner

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ