ዋና ገጽ መጣጥፍ
 
መጣጥፍ - Articles

ግልጽ ደብዳቤ (ፀሐይ አሳታሚና ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ) – (ሊያነቡት የሚገባ) Print E-mail
User Rating: / 4
PoorBest 

ክፍሌ ሙላት (የኢነጋማ ፕሬዝዳንት) - በግል

ሲሞላልኝ በሳምንት ካልሆነልኝ ደግሞ በአስራ አምስቱ ሰላምታዬን ካሉበት የማደርሳቸው ወዳጆች አሉኝ።  ለአገር ምድሩ ሳይሆን በጣት የሚቆጠሩ። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሙያ ባልደረባዬ ኤልያስ ወንድሙ ነው። ትውውቃችን የመንገድ ላይ አይደለም። የኔዎቹ የነፃ ፕሬስ አባላትና የሃገሬ ሰላም ወዳድ ኃይሎች በግፈኞቹ የሕወሃት አባላትና ሹመኞች የሚሰደዱበት የሚታሰሩበት ብሎም የግፍ ፅዋ የሚቃመሱበት በእነዚያ የትግል፣ የፈተናና የፍልምያ ዓመታት የልብ ወዳጅና ለእውነት የቆሙ በመብራት በሚፈለጉበት የወያኔ የግፍ ዘመናት። ዛሬም ይህ ሐቅ ገሃድ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...
 

“ሸቦ ግቢ እንገናኝ” ሊቀር ነው (ግርማ ደገፋ ገዳ) Print E-mail
User Rating: / 3
PoorBest 

ሆላንዶች አበባ ይወዳሉ። ወንጂ ውስጥ ያላመጡት አበባ የለም። በተለይ ሽቦ ግቢ ውስጥ ከሆላንድ የመጡ አበቦችና ዛፎች በብዛት ይታያሉ። ቤታቸውና ቢሯቸው ዓይን በሚማርኩ ልዩ ልዩ አበቦች የተከበበ ነው። ሽቦ ግቢ ያደጉ ያካባቢያችን ልጆች፣ ማለዳ ከእንቅልፋቸው ተነስተውና መስኮታቸውን ከፈት አድርገው፣ እነዚያን ውብ አበባዎች እየተመለክቱ፤ “Today is a beautiful day” ይላሉ ብለን እናስባለን። (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

 

ጭንቀት የወለደው የጦርነት ነጋሪት (በላይ ለገሰ) Print E-mail
User Rating: / 2
PoorBest 

መቋጫ የሌለው የኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ አ ንዳ በአፍሪቃ አህጉር ተወዳዳሪ የሌለው የተራዘመና የተወሳሰበ አውዳሚ ጦርነት ቁጥር ስፍር የሌለው የኢትዮጵያውያን ህይወት በልቷል፣ ብዙ ንብረትና  ብት አውድሟል፣ ባጠቃላይ በኤርትራ ከርሰ ምድር የኢትዮጵያውያን አፅም ያልተቀበረበት መሬት የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለምንበብ ይህንን ይጫኑ)

 

የጎጠኝነት አጥሩ እየተሰበረ … የተስፋ ጎህ እየቀደደ ነው (በዳኛቸው ቢያድግልኝ) Print E-mail
User Rating: / 1
PoorBest 

አማርኛና ኦሮምኛ ህብር ፈጥረው የአየር ሞገድ እየሰነጠቁ በጆሮአችን እየተንቆረቆሩ ነው። ፓልቶክ በሚሉት ዘመን አመጣሽ መገናኛ። …አብሮነታችን ያስከብረናል ነጻነት ለሁሉም ሲሆን ያኮራል፣ አብረን ስንሆን ያምርብናል የሚሉ አረፍተነገሮች ከየአቅጣጫው ይሰማሉ። ኢትዮጵያ በኦሮሞ ልጆችም የደም ክፍያ አገር ሆና የቆመች የነጻነት ተምሳሌት እንጂ ኦሮሞ እንደ ህዝብ የማንም ባርያ አልነበረም። (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለምንበብ ይህንን ይጫኑ)

 
«StartPrev12345678910NextEnd»

Page 1 of 102

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 


ኢሳትን ይርዱ!


በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ