ደም ያለበት ጳጳስ (የመነኩሴው ደም ይጮኻል!) ከምዕመን (ናይሮቢ - ኬንያ) መስከረም 1999 ዓ.ም. ከዘፍጥረት ዓለም - ከኦሪት ትዕዛዛቱ … “አትግደል” … ነበር ቃሉ - አንደኛው ከአሥርቱ፤
እግዚኦ ማኅረነ ክርስቶስ …! ነፍሰ-ገዳይ ሲሆን ጳጳስ … ያውም “ብፁዕ ወቅዱስ …”
(… ቃለ-ክርስቶስ ከጥንት የምናውቀው ሳዑል ወደ ጳውሎስነት ሲቀየር ነው፤ በኛስ ዘመን ጉድ መጣብን ጳውሎስ ሳዑል ሲሆንብን!!) … የመነኩሴው ደም ይጮኻል - የፈሰሰው ከታቦቱ ስር የሰማዕትነት ዋጋ - እማይዘነጋ ለዘወትር!
… ንስኀ ሳይገባ ለራሱ ሳትማር ተኮናኝ ነፍሱ እንዴት ሊያስተምረን ነው ጳጳሱ?!
አባታችን ሆይ የሰማዩ - በቃ! በለን አሁንስ “ነፍሰ-ገዳይ” ጳጳስ እየዞረ - ምናለ ታቦት ባያረክስ? አቡነ ዘበሰማያት … - ኢትዮጵያን ይቀር በላት ነፍሰ-ገዳይ ጳጳስ - ዳግም እንዳይነግሥባት! አቤቱ ኧረ ተለመነን!? ለዘላለም ዓለም አሜን!!!
ከምዕመን (ናይሮቢ - ኬንያ) መስከረም 1999 ዓ.ም.
|