|
ፋሲካ ፊልጶስ - ከሆላንድ (
This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it
) በጊዜ ሰንሰለት - በጊዜ ቀመር ወቅት አልፈህ የምትመጣው ሁሌም ዓመት - በዓመት የሙታን ትንሳዔ ታላቁ ዓውደ - ዓመት ”የኩዳዴ መፍቻ” እንዴት ነህ ፋሲካ በአንተ ያፈረ አለወይ ወይስ የተመካ? ...
ለማን ዛሩ ወርዶ ሆነለት ’ጆከር’ ማንስ ተነጅሶ ዞረበት ’አኪር‛ … እነማን አፍርሰው እነማን ጰጰሱ እነማን ተሽረው እነማን ነገሡ እነማን ተገለው እነማን ተርፍዋል እነማንስ ጠፍተው እነማን ለምተዋል እነማን ሄደው እነማን መ’ተዋል እነማንስ ከድተው እነማን ታመኑ ተጠየቅ ፋሲካ በዓውደ - ዓመት ዘመኑ? ... ፎቅ በፎቅ ገብቶ አዲስ ቪላ ሠርቶ ወይም መርጦ ገዝቶ … በአዲስ ልብስ አጊጦ አምሮ ተሽቆጥቁጦ … ሰንጋ ፍሪዳውን - በግ ዶሮውን አርዶ ጮማ ሥጋ ቆርጦ - በጠጅ በውስኪ በጠላ አወራርዶ … ስንቱ ሰው ፈሰክ በቀዬ ባድባሩ ስንቱስ ጾም አደረ - ስንቱስ ተሳደደ በገዛ ሀገሩ። ቤተሰቡን አ’ቶ - ቤት ንብረቱ ፈርሶ በወገን ትዝታ ውስጥ ልቡ ታምሶ በሰው ሀገር ምድር በስደት ‘ካምፕ’ ኑሮ በኀዘን በመከራ - በእዬዬ - በእሮሮ ስንቱ ውሎ አደረ የባዕዳ እጅ ልሶ ዓውዳ - ዓመትህ እምባውን አፍስሶ። ከሙያ ጉሮሮው - ከሥራው ተነስቶ የጎጆ ቅልሱን የእጁን ተቀምቶ ‘በፕላስቲክ’ ጣራ በጎዳና ኑሮ ስንት ወገን ፈሰከህ አ’ቶ ‘መናኛ’ ዶሮ። እነማን ታስረው - በእነማን ተግዘው ያለፍርድ ዘብጥያ - ከርቸሌ ወርደው በዕለተ ፋሲካህ … በዕለተ ዓውደ - ዓመትህ … በሃሳብ በትካዜ በትዝታ ዋለ በ’ውነት ትንሣዔ ነው - በዓል ነወይ እያለ። የነማን አባቶች - የነማን እናቶች የነማን ወንድሞች - የነማን እህቶች የነማን ልጆች - የነማን ወገኖች … በየስርቻው ... በየጎዳናው ተንቀው ... ተዋርደው ተረግጠው ... ተጥለው ሲለምኑ ዋሉ በዕለተ ዓውደ - ዓመትህ ማንስ ሆነ መጽዋች ዘካሪ በስምህ። ፋሲካ ያ’መት ነህ ብታልፍ ትመጣለህ ምን ‘አኪር’ ይዘህ ነው ምን ‘ካርታ’ ስበን ነው ደ’ሞ የዛሬ ዓመት የምንገናኘው ??? ...
ፊልጶስ - ከሆላንድ (
This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it
)
|