|
ዓባይ ብርዞ - ከፍራንክፈርት
This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it
ዓባይ የምድረ ንስር ሲሳይ የጥቁር አፈር ሽታ የሰሜን ተራራ ክፋይ የከርሰ ጦቢያ ውልድ የምህተዓመት ፍሰት የሥልጣኔ ዓሃዱ የሰብህና ጅምር እውነት
የጠመዝማዛ ጉዞ ዜማ የውሃ ሳቅ ትርዒት የእምይ ጦቢያ እምብርት ማራኪ ቀለም ውበት የእንዶድ ፏፏቴ ዝላይ የአምቁ ጢስ ምትሓት የሕዋ ምድር ተምሳል የማይጠገብ ትዕይንት ባለከበረው ድንጋይ ደንደሳም ባለደለል ብድግ ወረድ ዘርገፍ ፈንጠር ጎምለል ከብለል ጦብያ እናትህን እያት አንገትህን አርገው ዞር ሸክምህን አራግፈህ አስተውላት ባንተ ትታደግ ትጦር የባጎረስኩኝ እጄን ተረት ያድካሚው ጉዞ ምላሽ የትውልድ ስጋት ፈተና አትሆንም ፍፁም ጭራሽ አረንጓዴውን ራዕይ የነፍስ አድኑን ተስፋ በተቀደሰ ምድርዋ ላይ ታደርገዋለህ ይፋ
ብርዞ ከፍራንክፈርት
This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it
|