| ጥላ ከለላችን (በኩረ ይጥና) |
|
| Art - ግጥም | |
|
ጥላ ከለላችን በኩረ ይጥና ሚያዝያ 2001 ዓ.ም. / አፕሪል 2009 - ዳላስ ( This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it ) ጥላዬ ጥልዬ ብለን ስንጣራ - ከወዲያ ከወዲህ፤ ከሰውነታችን ካፋችን ሳትጠፋ - ሁሌም ስናነሳህ፤ ሰምተንህ ሳንሰለች - አይተንም ሳንጠግብህ፤ እንዲህ እንደ ዋዛ - ምነው ማሽለብህ፤
ላፍታ ሳናወራህ፤ የሆዳችንንም - ሳናጨዋውትህ፤ ሌላው እንኳን ቢቀር - ደህና ሁን ሳንልህ፤ አስደንጋጩ ዜና በዕለተ-ትንሳዔ - ተሰማ ህልፈትህ፤ “ጥላ-ከለላችን” ማሸለብክን ሰማን - እስከ መጨረሻህ፤ ጥላሁን ገሠሠ የአርቲስቶቹ ቁንጮ - የሙዚቃው ንጉሥ፤ በምትሄድበትም - በእግዚያብሔር ቤት ንገሥ፤ ከአብረሃም - ከሣራ - ከጻድቃን ጋር ተንፍስ፤ ዳግም እስክናይህ - እኛም ተራ ደርሶን ትተህ በሄድክልን - በሙዚቃዎችህ የጠላሽ-ይጠላ፣ የሕይወቴ-ሕይወት፣ ስትሄድ ስከተላት፤ ... ያሳለፍነው ዘመን፣ አልቻልኩም፣ ኡኡታ፣ ያም ሲያማ፣ … ኧረ-ስንቱን እንቆጥራለን እንዲያው በደፈናው - ሁሉን እየሰማን፤ እስከዘላለሙ እናስብሃለን፤ እንግዲህ “ጥልዬ” ከጨ ከንክ - ካመረርክ፤ ዳግም ላትመለስ - ለዘለዓለም ከሄድክ፤ አምላክ ለቤተሰብ - ለኢትዮጵያም ህዝብ መጽናናቱን ይላክ፤
በኩረ ይጥና ሚያዝያ 2001 ዓ.ም. / አፕሪል 2009 - ዳላስ ( This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it ) |
|