Home ኪነ-ጥበብ ግጥም ጥላ ከለላችን (በኩረ ይጥና)
 
ጥላ ከለላችን (በኩረ ይጥና) Print E-mail
User Rating: / 2
PoorBest 
Art - ግጥም Poem

ጥላ ከለላችን

በኩረ ይጥና ሚያዝያ 2001 ዓ.ም. / አፕሪል 2009 - ዳላስ ( This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it )

ጥላዬ ጥልዬ ብለን ስንጣራ - ከወዲያ ከወዲህ፤

ከሰውነታችን ካፋችን ሳትጠፋ - ሁሌም ስናነሳህ፤

ሰምተንህ ሳንሰለች - አይተንም ሳንጠግብህ፤

እንዲህ እንደ ዋዛ - ምነው ማሽለብህ፤

 

ላፍታ ሳናወራህ፤ የሆዳችንንም - ሳናጨዋውትህ፤

ሌላው እንኳን ቢቀር - ደህና ሁን ሳንልህ፤

አስደንጋጩ ዜና በዕለተ-ትንሳዔ - ተሰማ ህልፈትህ፤

“ጥላ-ከለላችን” ማሸለብክን ሰማን - እስከ መጨረሻህ፤

ጥላሁን ገሠሠ የአርቲስቶቹ ቁንጮ - የሙዚቃው ንጉሥ፤

በምትሄድበትም - በእግዚያብሔር ቤት ንገሥ፤

ከአብረሃም - ከሣራ - ከጻድቃን ጋር ተንፍስ፤

ዳግም እስክናይህ - እኛም ተራ ደርሶን

ትተህ በሄድክልን - በሙዚቃዎችህ

የጠላሽ-ይጠላ፣ የሕይወቴ-ሕይወት፣

ስትሄድ ስከተላት፤ ...

ያሳለፍነው ዘመን፣ አልቻልኩም፣ ኡኡታ፣ ያም ሲያማ፣ … ኧረ-ስንቱን እንቆጥራለን

እንዲያው በደፈናው - ሁሉን እየሰማን፤

እስከዘላለሙ እናስብሃለን፤

እንግዲህ “ጥልዬ” ከጨ ከንክ - ካመረርክ፤

ዳግም ላትመለስ - ለዘለዓለም ከሄድክ፤

አምላክ ለቤተሰብ - ለኢትዮጵያም ህዝብ

መጽናናቱን ይላክ፤


 

በኩረ ይጥና ሚያዝያ 2001 ዓ.ም. / አፕሪል 2009 - ዳላስ ( This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it )

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ