|
ዓባይ ገ/ኢ. ጐርፉ ፀሐይ ዳመናው ቁልጭ-ልጭ በጋው አልፎ ክረምት ገባ፣ ዳመናው ብልጭ-ልጭ ነጐድጓዱ ነጐደ፣ መስከረም እስኪጠባ ወንዙ ሄዶ ገደብ አልባ ... አባይ ተዥጐደጐደ!
ዝናቡ ዘንቦ-ዘንቦ
መሬቱን ተረተረው፣ ግድብ የለ ገንዳ፣ ገንቦ አፈሬን አጥቦ-አጥቦ ቁልቁሊት አምዘግዝጎ መሬቱን ሸረሸረው ግብፅ ወስዶ ሊከምረው ወሰደው ጠራርጎ ... ማነው ፈረሰኛው ዘምቶ ከወድያ ማዶ ከባዕድ ምቀኛው የሚመልስ ያንን ያገሬ አፈሩን፣ ባሕር-ዛፉ ማገዶ አለቀ ነድዶ-ነድዶ! አንድ በሉልኝ እንጅ ወንድም ጋሼስ የለም ወይ? ስሞትስ አያይም ወይ? ይህ መቸውም አይበጅ በግብፁ በጠላቴ ማቀቀ አካላቴ፣ ተቀጨ ልጅነቴ …
ገ/ኢ. ጐርፉ www.ethiopianhcc.org 9852 Stanford Av., Garden Grove, CA. 92841
|