ዋና ገጽ ኪነ-ጥበብ ግጥም “እኔን አፈር - ይብላኝ” (አባ ቤክሲሳ)
 
“እኔን አፈር - ይብላኝ” (አባ ቤክሲሳ) Print E-mail
User Rating: / 17
PoorBest 

“እኔን አፈር - ይብላኝ”

አባ ቤክሲሳ This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it

ብርቱ!

ወላፈን ሲጋረፍ ሙቀት ሲበረታ

ተመልካች ሲያላዝን ለፍርሃት ሲረታ።

ከተንቦለቦለው ከግለቱ መሃል

አሳልፋ ሰጥታ ራሷን ለነበልባል።

 

 

ከሞት ያዳነችኝ

ነገን ያኖረችኝ

 

እሳት የበላትን

የእውነቷን ‘እቴቴ’ን -

እህቴን መሰልሽኝ።

 

 

በርቺ ብርቱ-ከኔ!

አትታመሚብኝ አትድከሚ እንደሰዉ

ኑሪ ለዘላለም ሞት-ሽን ልውረሰው።

 

ዕብሪት በለስ ቀንቶት ሲተብት ንጉሡ

ከልጅሽ በልጦብሽ ቃልሽ ከነጦሱ፣

ዱራ ሲመፃደቅ እኩይ ባንቺ ሲናኝ

ቆሞ ታዛቢውን “እኔን አፈር-ይብላኝ”።


አባ ቤክሲሳ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 


ኢሳትን ይርዱ!


በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ