ዋና ገጽ ኪነ-ጥበብ ግጥም አባ ዜና (መቅደስ- ከካናዳ)
 
አባ ዜና (መቅደስ- ከካናዳ) Print E-mail
User Rating: / 10
PoorBest 

አባ ዜና

መቅደስ- ከካናዳ

ካህናተ ሥልጣን የተካነው፣

የእምነት በጎቹን ሰብሳቢዉ፣

ቀናውን መንገድ ተናጋሪው፣

ታዛዥ ትሁቱ ለፈጣሪው።

 

ያ የእምነት አርበኛ ጀግና፤

በቃሉ አዳሪው አባ ዜና፣

ይመስከርለት ምግባሩ

ይነገርለት ታምሩ፣

ዓለም ሳትገዛው መኖሩ፣

ሳያስጨንቀው ሞገስ ክብሩ።

 

ህዝበ ሲያትል ይናገር፣

ስለ አባ ዜና ቁም ነገር።

 

ታምራቸውን የቀመሰ፣

መስቀል ከእጃቸው የዳሰሰ፤

እኛም መስካሪ እንሆናለን፣

ስለ ገድላቸው እናወራለን።

 

ስም አልባ ሆነን ብንቆይም፣

ጠላት መድረሻ ቢያሳጣንም፤

አዝመን ብንቆም ባንወድቅም፣

አቡነ ዜና ስም ሰቶናል፣

በፀደንያ ክብር ሰይሞናል፣

ትጉህ እረኛን አድሎናል፣

ቀናም እንድንል አድርጎናል።

 

የእምነት ገበሬው አባ ዜና፣

ልጆቹን ሰብሳቢው ልበ ቀና፣

በሄደበት ሁሉ ቅርስ እየተወልን፣

ቤት አልባ እንዳንሆን መቅደሱን ሰራልን።

 

ያ የእምነት አርበኛ ጀግና፣

በቃሉ አዳሪው አባ ዜና፤

በዓላማው ፅናት ተጠብቆ፣

ቢሰደድ እንኳ ካ’ገሩ እርቆ፣

ዳዊት መቁጠሪያዉን ሰንቆ።

 

መንፈሱ ግን ትኖራለች፣

ላገር ምድሩ ትቆማለች፣

የሰላም አዋጅ ታዉጃለች፣

በጌታ ቀኝ ትነግሳለች።

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 


ኢሳትን ይርዱ!


በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ