ዋና ገጽ ኪነ-ጥበብ ግጥም ዘነበች (ጭራቀረሽ)
 
ዘነበች (ጭራቀረሽ) Print E-mail
User Rating: / 6
PoorBest 

Artist Zenebech taddese (ዘነበች ታደሰ / ጭራቀረሽ)ዘነበች (ጭራቀረሽ)

የራስን ሞት ሲሞት፣

“... የሥራ ድርሻዬን አርቀው ይመልከቱት፣

አርባ ዓመት ይሆናል በመድረክ የኖርኩት፣

ደግሞም ይረዱልኝ በጥልቀት አስበው፣

ተውኔትና እውነታን ጎን ለጎን አስቀምጠው።

 

ታሪክ መዝግቡልኝ ልፋቴን ድካሜን፣

አርባውን ዓመታት የሙዚቃ ዓለሜን፣

መድረክ ላይ ስገባ ልብ-ወለድ ትረካ፣

ጨካኝ ወይ ሩህሩህ ለተውኔት ውከላ፤

“ጭራ ቀረሽነት” ደስታና ትካዜ፣

ትዕዛዝ መፈፀም ነው ያለብኝ አባዜ፣

ሙች ሲሉኝ ሞቼ ከመሬት ስዘረር፣

አታካራ የለኝ ጭቅጭቅ ግርግር፤

ታዲያ ትርዒት ሲያበቃ ከሞት ተነስቼ፣

ከተመልካቹ ፊት ቆሜ ተደስቼ፤

ጭብጨባ ታጅቤ፣ ጩኸትና ኹካታ፣

እላበስ ነበር ሣቅና ፈገግታ፤

ዛሬ ግን ሌላ ነው በደንብ ተረዳሁት፣

ደግሞ መቆም የለም የራስን ሞት ሲሞት ...”


በላይ ጎጃሜ

(ማርች ወር 2007 እ.ኤ.አ. ላረፈችው ዘነበች ታደሰ /ጭራቀረሽ/ ሀገር ፍቅር ሙት ዓመት መታሰቢያ)

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 


ኢሳትን ይርዱ!


በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ