|
Art -
ግጥም Poem
|
|
ውሸት ነገሠ ዳግማዊ ዳዊት
This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it
መስቀል አደባባይ - ሀዝባችን ተጠርቶ ሕፃን ሽማግሌው ባልቴት እና አዋቂው - ግልብጥ ብሎ ወጥቶ
የክብር እንግዶች - ከአውሮጳ ከእስያ ከጎረቤት ሀገር - ጅቡቲ ኬንያ
የአሜሪካው ቆንሲል - ሚስተርም ተገኝተው ጳጳሱ ተጠርተው - ካህናት ቀድሰው ቅባ-ቅዱስ ፈልቶ - በአናቱም አፍስሰው አክሊል ተደፋለት - እምቢልታ ተነፋ ህዝብ ሠገደለት - ሥልጣን ክብሩ ሰፋ ከበሮ ተመታ - ሆታውም ቀለጠ - እልልታ ተሰማ ውሸት ንጉሥ ሆነ - ስርቆት አልጋ ወራሽ - በሀገሬ ከተማ። እናም የእኛ ሰፈር - ትልቅ ሽማግሌ አንቱ የተባሉት - ትናንት እና ዛሬ በቁርባን ያገቡት - በክርስትናቸው ይኸው በአደባባይ - ሲዋሹ ያዝናቸው።
መቸ ይኸ ብቻ - ሆነና ነገሩ በሃሰት ተከስሰው - ተሰማና ፋይሉ ደግነት ቅንነት - እስር ቤት ገቡ አሉ። እንግዲህ ምን ይሉ - ዘመን ተቀየረ ውሃ ሽቅብ አይፈስ - ሲባልም ነበረ ዘመን ተገላብጦ - ውሸት ተከበረ።
ኑሯችን ሆነና - ከደሃው ቀምተን እውነትን ንቀነው - ውሸትን አንግሠን ወደፊት ለመሄድ - መራመድ አቃተን።
ዳግማዊ ዳዊት
This e-mail address is being protected from spambots, you need JavaScript enabled to view it
የካቲት 2002 ዓ.ም. |