Home ኪነ-ጥበብ ግጥም እስረኞች (በፈቃዱ ሞረዳ - ስለቴዲ አፍሮ)
 
እስረኞች (በፈቃዱ ሞረዳ - ስለቴዲ አፍሮ) Print E-mail
User Rating: / 20
PoorBest 
Art - ግጥም Poem

እስረኞች

በፈቃዱ ሞረዳ (ስለቴዲ አፍሮ)

 

ምንድነው ጫጫታው፣ ሆይ ሆይታ ቱማታ?

“እገሌ ነፃ ነው፣ እንትና ተፈታ”

ጎበዝ ረጋ በሉ፣ ሠርክ አትሳሳቱ

ማንም አልተፈታም፣ ሙሉ ነው ’ስር ቤቱ።

 

በዘብጥያው መሃል ልዩነቱ ያለው

አንደኛው መጥበቡ፣ ሌላው መስፋቱ ነው።

 

“እገሌ ተፈታ፣ እገሊትን ፍቱ!”

እናንት “እስረኞች” ቧልት አትፎትቱ።

ባፀደ ጠብመንጃ በታገተች ሀገር

“ፍቺ” ብሎ ቆሳ፣ “ነፃ” ብሎ ነገር።

 

ወጪና ገቢውን ይቅር አትቁጠሩ

የተኛው ይቀስቀስ፣ ላልሰማው ንገሩ

ትጉ ለተባብሮ፣ አፀዱን ስበሩ።


 

በፈቃዱ ሞረዳ (ስለቴዲ አፍሮ)

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ