ይኑሩ አይሙቱብን (ላቶ መለስ - አትክልት አሰፋ)

Share

አትክልት አሰፋ

ትንሽ ይቆዩ እንጂ   ጥቂት ይኑሩልን፣

ባሉበት ሰንብተው ስቃይ ተካፈሉን።

ጭንቀትን ይወቁት በሞቴ ይኑሩ፣

ይቅመሱት ባሉበት እንዲሁ እንዳሉ፤

ወደ ላይ አይሂዱ ወደሰላሙ አለም፣

እዚያ ከሄዱማ ምንም ነገር የለም፤

ወደዚያም አይሂዱ ወዲህም አይምጡ፣

ባሉበት ቦታ ላይ እዚያው ይቀመጡ

በፍትህ ፊት ቆመው በፍርድ እስኪቀጡ።

Share
Template by A4