|
እኛ ግን ለውጥ የለን ስሜነህ ታምራት (ከስዊድን) ከአዲስ ዘመን ጋራ - አዲስ ተስፋ ሳይወለድ የታሰረው ሳይፈታ - የተፈታው ሳይራመድ ተቻችሎ ለሀገር መሥራት - እንደባህል ሳይለመድ አብሮ መብላት አብሮ መጨፈር - ምን ሊፈይድ ምንስ ሊያመጣ - ምንስ ሊወስድ።
ለእግዚአብሔር ሠላምታ ደንታ የማይሰጠው ፍቅርና አንድነት ጨርሶ የሌለው ዘመኑ ቢለወጥ ምን ባንድ አስጨፈረው?
ህዝበ-ቃል ተከብሮ - ህዝበ-ኃይል ሲረታ ተፈችው ሲራመድ - እስረኛው ሲፈታ መዝለልስ ያኔ ነው - መጨፈር እስክስታ። ዘመን ተለወጠ - እኛ እንጅ የቀረን ለውጥን እየፈለግን - እኛ ግን ለውጥ የለን።
ስሜነህ ታምራት (ከስዊድን)
This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it
|