ዋና ገጽ ኪነ-ጥበብ ግጥም ስልትህን ቀይር (ሚሊዮን ጎሣዬ)
 
ስልትህን ቀይር (ሚሊዮን ጎሣዬ) Print E-mail
User Rating: / 6
PoorBest 

ስልትህን ቀይር

ሚሊዮን ጎሣዬ (ከኦስሎ - ኖርዌይ)

የእውነት ምርጫ ቢያከናውን

ተሸናፊ መሆኑን እናውቃለን

ግን ይህን ድራማውን

ለነጭ ለጋሾች ማምታቻውን

 

ተሸንፎ አሸነፍኩ ማሰኘቱ

በአዋጅ ነጋሪ ማስወራቱ

አይቀሬ ነው መዋሸቱ

ሳይመረጥ ተመረጥኩ ማለቱ

 

እናም ያገሬ ወጣት

ድምፅህን ቀምተው ሲወስዱት

ሳትመርጣቸው አሸነፍን ሲሉ

በየሚዲያው ሲገዘቱ ሲምሉ

መብትህ ሲገፈፍ ቢያምም

አዘልሎ አደባባይ ቢያስወጣም

 

ስልትህን ቀይረህ ታገለው

ደም ሳይፈስ እንደቀደሞው

አትስጥ ደረትህን ለጥይት

ወያኔ ውሃ መርጨት ላያውቅበት

ከጠመንጃው አፍ ሞት እንጂ

አስለቃሽ ጭስ ላይወጣበት

ለሱ እንደው ደም ማፍሰሱ

የሚወደው ልማዱ ነው ሱሱ

 

ፈቅዶልህ አደባባይ አያስወጣህ

ቤትህ ሆነህ ዘዴ ካላመጣህ

ጀንበሩ ስትጠልቅ ጠብቀህ

እሪ ብለህ አቅልጥ ጩኸትህን

ለዓለም አሰማ በደልህ

ወይም ሌላ ዘዴ ፈጥረህ

አሳውቅ እንጂ ድምፅህ መዘረፉን

ወገን አይሙት አደራህን


ሚሊዮን ጎሣዬ

ኦስሎ - ኖርዌይ

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 
Banner

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ