ዋና ገጽ ኪነ-ጥበብ ግጥም ርግባችንን እንታደጋት (ለብርቱካን ሚደቅሳ)
 
ርግባችንን እንታደጋት (ለብርቱካን ሚደቅሳ) Print E-mail
User Rating: / 2
PoorBest 

ርግባችንን እንታደጋት!!

(ለብርቱካን ሚደቅሳ)

Free Birtukan Mideksa

 

የወይራ ቅርንጫፍ አንግባ - መልዕክተ-ሕይወትን ልታበስር፣

የዘንባባ ዝንጣፊ አዝላ - ለፍትህ፣ ለሠላም ... ለፍቅር፣

የሁሉን ልብ ስታማልል - የሠላም የእኩልነት ዓርማችን፣

አየሩን ቀዝፋ ስትበር - ንፅህት፣ ፀዐዳ ርግባችን፤

በጨለመው ”መርከብ” ታክቶ - ብርሃን ሕይወት የናፈቀው፣

ላሳየችው ብሩህ ተስፋ - ሀገር ምድሩ ደስ ሲለው፤

እባብ ብቻ ቂሙን ቋጥሮ - ሊያሰናክል ከጉዞዋ፣

በጨለማ ጠፍንጓት - ስለበዛ መከራዋ፣

ያገር አድባር ሳይቆረጥ - ሳይመጣብን ከንቱ መዐት፣

አቤት! አቤት! እንላለን - ርግባችንን እናድናት!!

ጌታቸው አበራ

ሚያዝያ 2002 ዓ.ም.

(አፕሪል 2010 እ.ኤ.አ.)

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 
Banner

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ