|
በ’ንባዬ ልሸኝሽ ! አሥራደው (ከፈረንሳይ) በሰው አገር ሆነሽ አገር እንደራበሽ፤ እናት አባት ናፍቀሽ፤ ወንድም እህት ናፍቀሽ፤ ብለን ስንጠብቅ አገር ትገቢያለሽ፤ በዚያው ቀረሽ ምነው ናፍቆትሽን ይዘሽ ? ጥቂትም ሳታርፊ በሰው አገር ለፍተሽ፤ በሥጋ እንደበረርሽ በነፍስሽም ቀጠልሽ፤ እቴ ያገሬ ልጅ ከልቤ አዘንኩልሽ፤ ሌላ ምን ሃብት አለኝ በ’ንባዬ ልሸኝሽ :: በአይሮፕላን አደጋ ሕይወታቸው ላለፈ እህቶቻችን መታሰቢያ
|