ዋና ገጽ ኪነ-ጥበብ ግጥም እስቲ ልጠይቅሽ (አሥራደው - ከፈረንሣይ)
 
እስቲ ልጠይቅሽ (አሥራደው - ከፈረንሣይ) Print E-mail
User Rating: / 20
PoorBest 

እስቲ ልጠይቅሽ

(አሥራደው - ከፈረንሳሣ)

አድምጭኝ ሀገሬ፤

መመኪያዬ ክብሬ፤

የ’ኔነት መግለጫ ክብርና ኩራቴ፤

የመኖሬ ትርጉም ፍቺ የሕይወቴ፤

ማረፊያ ጎጆዬ ሲደክም ጉልበቴ፤

እስቲ ልጠይቅሽ፤

ምትክ ለልጆችሽ፤

ላንቺ በደከሙ ላንቺ በሞቱልሽ፤

እነማንን ተካሽ?!

እነማንን ወለድሽ?!

 

በለጋነት ዕድሜ ገና በጨቅላነት፤

ላንቺ ልዕልና ብለው በተሰዉት፤

በነዛ ጉብሎች በነዛ ሰማዕት፤

በወጣት ልጆችሽ፤

እነማንን ተካሽ?!

እነማንን ወለድሽ?!

ሀገሬ ንገሪኝ እስቲ ልጠይቅሽ።

 

ከራሳቸው ሕይወት ላንቺ የሚያደሉ፤

ላንቺ የታመሙ ላንቺ የቆሰሉ፤

ላንቺ ዘብ በመቆም ላንቺ ተሰውተው፤

ተቃጥለው ላለፉ በፍቅርሽ ጧፍ ሆነው፤

ለክብርሽ እንደ ሰም ለተነኑ ቀልጠው፤

በነዚያ ልጆችሽ፤

እነማንን ተካሽ?!

ሀገሬ ኢትዮጵያ እስቲ ልጠይቅሽ ...

 

ጀግና ደራሲውን፤

መሃንዲስ ሐኪሙን፤

ቆፍጣና ወታደር ድንበር ጠባቂውን፤

ነጋዴ ገበሬ ተማሪ አስተማሪ፤

ሰዓሊ ተዋናይ ምሁር ሀገር መሪ፤

ዳኛ ዲፕሎማት፤

መሪ የኃይማኖት፤

ሁሉን አሰናብተሽ፤

ኧረ ለመሆኑ እነማንን ወለድሽ?!

እነማንን ተካሽ?!

ሀገሬ ንገሪኝ እስቲ ልጠይቅሽ ... 

 

መካሪ ዘካሪ ምሑር አስተማሪ፤

ጀግና ወቶ አዳሪ ድንበር አስከባሪ፤

ታሪክን ጠባቂ በሳል ሀገር መሪ፤

ቁም ነገር ከሠሩ ጥቂት ሳታስቀሪ፤

ሁሉንም ሸኝተሽ፤

ሁሉን አሰናብተሽ፤

እነማንን ወለድሽ?!

እነማንን ተካሽ?!

ሀገሬ ኢትዮጵያ እስቲ ልጠይቅሽ ...


 

ለአገራቸውና ለወገናቸው ቁም ነገር ሠርተው ላለፉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መታሰቢያ ትሁንልኝ። ታኅሳስ 24/ 2002 ዓ.ም. (January 2/ 2010) This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 
Banner

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ