ዋና ገጽ ኪነ-ጥበብ ግጥም ዱላ ቅብብል (በአቤል ካሳሁንና በማህሙድ ኢድሪስ)
 
ዱላ ቅብብል (በአቤል ካሳሁንና በማህሙድ ኢድሪስ) Print E-mail
User Rating: / 12
PoorBest 
ድንቅ ያፍሪካ አትሌቶች የሚሰሩት ስራ
መላውን ጥቁር ህዝብ እጅግ ስላኮራ፤

በየደረሱበት በየውድድሩ፣
ታሪክ እየሰሩ፣ ድል እያበሰሩ፤
የናት ምድራቸውን ስም ስላስከበሩ
               ለታላቅ ሽልማት
ወደ አፍሪካ አዳራሽ በክብር ተጠሩ።

ከዚያም ጋዜጠኛ- ተናግሮ አናጋሪ የወሬ ሱሰኛ፤
ወደ አንዱ አትሌት ቀርቦ
አድናቆቱን ደልጾ ድምጹን አለዝቦ፤
‘ጽናት በሚጠይቅ በረዥም ርቀት
ታሸንፋላችሁ ሁሌም ያለጭንቀት፣
አምስት ሽ አስር ሺው ውጤቱ ቢያረካም
ዱላ ቅብብሉስ ለምን አይሳካም?’
                በማለት ጠየቀ።

ታዋቂው አትሌትም በስሱ እየሳቀ
‘ቀን ከሌት በመስራት ጥረታችን ሰምሮ፣
                   ውጤታችን አምሮ
                    በስካሁን ድላችን
                    ረክቷል ህዝባችን
ዌል.. እንግዲህ ደግሞ ዱላ ቅብብሉን- ለመሪዎቻችን’
                                  ብሎ ተናገረ
                   በዚህ ንግግሩም ሪከርድ ሰበረ።
አቤል ካሳሁንና ማህሙድ እንድሪስ ካሳተሙት
‘ከ… እስከ’ የግጥም መድብል የተወሰደ

 

አዲስ ዜናዎችና ጽሑፎች

 
Banner

በጽሑፍ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ!

በማናቸውም ጉዳይ ላይ ያለዎትን ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ትችት፣ ግጥም፣ ልብወለድ፣ … በማይክሮሶፍት ወርድ ፕሮግራም በዩኒኮድ ፎንት ጽፈው ከራስዎ ኢ-ሜይል ሳጥን ጽሑፎትን አያይዘው በኢ-ሜይል አድራሻችን 

ethiopiazare@gmail.com ቢልኩልን ለሥራችን ቅልጥፍና ይረዱናል።

ኢትዮጵያ ዛሬ