|
ሀብታሙ አሰፋ የአቶ መለስ አስተዳደር ደጋግሞ እንደተናገረው የ97ቱ ምርጫ እንዳይደገም ቀዳዳዎችን ሁሉ ደፍኗል። እነዚህ ቀዳዳዎች የታወቁ ናቸው። ምርጫ እንዳይኖር የሚያደርጉ የአፈና እርምጃዎችን ነው። ይቃወሙኛል የሚላቸውን ሁሉ በሞትና በእድሜ ልክ እስራት የሚቀጣበት የፀረ-አሸባሪነት ሕግ አውጥቷል። ከዚህ አልፎም ሕጉ በነማን ላይ እንደሚሰራ እነ ጀነራል ተፈራ ማሞ በፈጠራ ወንጀል በዚሁ አዋጅ መሰረት ተፈረዶባቸዋል። በ97ቱ ምርጫ በገለልተኝነት የታዘቡ የሲቪል ማህበረሰቡን የሚወክሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ፀጥ የሚያደርግ አዋጅ ወጥቷል። የፕሬስ ነፃነት ተስፋ ጭምር እንዲጨልም የዘጋውን ዘግቷል። ያሰጉኛል የሚላቸውንም የቀሩትን ለይቶ ተራ በተራ ለመጨፍለቅ ዘመቻ ይዟል። ተቃዋሚዎችን ለመከፋፈል የጀመረው ዘመቻ ከቅንጅት ውህደት ተቃውሞ ተነስቶ አጋር ተቃዋሚዎች እስከማፍራት ሄዷል። |
|
ሙሉውን አስነብበኝ ...
|